በአ.ብ.ክ.መ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው የግዥ ዕቅድ መሰረት ሎት -1 የጽ/መሳሪያዎችን፣ ሎት 2 የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3 ጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 5– ክሎሪን፣ ሎት 6 ህትመት፣ ሎት 7 የግንባታ ዕቃዎች፣ ሎት 8 ጀኔሬተር ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአ.ብ.ክ.መ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ጎዛምን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአ.ብ.ክ.መ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በያዘው የግዥ ዕቅድ መሰረት ሎት -1 የጽ/መሳሪያዎችን፣ ሎት 2 የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3 ጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 5– ክሎሪን፣ ሎት 6 ህትመት፣ ሎት 7 የግንባታ ዕቃዎች፣ ሎት 8 ጀኔሬተር ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የግዥ መጠናቸው 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ጎዛምን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር-2 ወይም ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) እያንዳንዱ ሎት ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በማስላት በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በሂ-1 ገቢ አድርጐ አንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሲ.ፒ.ኦ ብሎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑን በተመለከተ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11:30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3:30 ታሽጎ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድኑ ተዘጋጅቶ የተሠጣቸውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የይዘት ለውጥ ወይንም ማሻሻያ ሳያደርጉ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣ ሆኖም የተሠጠ ሰነድ ላይ የግልፅነት ማብራሪያ ካስፈለገ ደውለው ወይም በአካል ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማቸውን በማድረግ፤ ማህተም በመርገጥና በፖስታ በማሸግና ፖስታው ላይ አድራሻ በመፃፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር-8 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ የተፈላጊነት ደረጃ/ በግዥ ቡድናችን ከተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሠነድ ላይ ማየት ይችላሉ። ለሚገዙ ግዥዎች ናሙና የግዥ ቡድናችን ቢሮ ከላይ የሚቀመጥ ይሆናል።
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት የጨረታ ውድድሩን በሎት ዋጋ (በጥቅል ዋጋ ድምር) የሚያወዳድር ሲሆን ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች አሸናፊ ሆኖ የሚመረጥ ይሆናል፡፡
- የዕቃ አቅርቦት ጥራት ችግር እንዳይከሠት በሚመለከታቸው ባለሙያዎች የተረጋገጡ የዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል። ነገር ግን የጥራት ጉድለት ያለበት ዕቃ የሚመለስ መሆኑን አንገልፃለን።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 30 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር-8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581780130/0587711422 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ጎዛምን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ደብረ ማርቆስ
