በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል 2ኛ ዙር ጥቅል ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል 2ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ማለትም
- የጽሕፈት መሣሪያ፣ 2. የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ 3. አላቂ የጽዳት ዕቃዎች 4. የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱን ለአንዱ ሎት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ይህን ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ከሰኞ-አርብ) በሥራ ሰዓት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት ለየ ብቻ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸዉ
- ጽህፈት መሳሪያ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
- ደንብ ልብስ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
- ጽዳት እቃዎች 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
- ደንብ ልብስ ስፌት 7,000 (ሰባት ሺህ ብር)
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን መሥሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚለው ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም እና በመፈረም፤ የቴክኒካልና የፋይናንሽያል ኦርጂናል በአንድ ፖስታ ላይ ኮፒያቸውን ለብቻ በሌላ ፖስታ በማሸግ ለአንድ ሎት ሁለት ፖስታ በአጠቃላይ ሁሉንም ሎቶች ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ዓይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በየ ሎቱ ከፋፍለው ለየብቻ በማይቀደድ እቃ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው ናሙና ከላቀረቡ ጨረታ መሳተፍ አይችልም ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመሆኑም ከተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ውጪ የሚቀርቡ ማንኛውም የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ወጪ በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 07 ፋ/ጽ/ቤት ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተገኙባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤት ጋር የግዥ ውል ስምምነት በመፈራረም ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ዕቃዎችን ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ እና 20 % ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ከመገናኛ ወደ ሰአሊተ ምህረት ቤ/ክ በሚወስደው መንገድ ጉርድ ሾላ በሻሌ ሆቴል ፊት ለፊት ወይም
በስልክ ቁጥር 011-812-24-86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት
