Tender Detail

Tender Details


የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ UPS ባትሪዎች፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛዎች፤ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ዲክሰን ብረት መደርደሪያዎች፣ ካውንተር እና ኬጂ ከነ ግራናይቱ ጋር፣ ንቃይ የብረት በሮች፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የጥበቃ ቤቶች፤ የጣራ ቆርቆሮዎች፤ የባንኩ የቅርንጫፎች ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፤ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፤ አሮጌ ጋዜጣዎች፣ የኔት ወርክ ኬብሎች (UTP) እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር FA- 04/2025/26)

 

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ UPS ባትሪዎች፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛዎች፤ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ዲክሰን ብረት መደርደሪያዎች፣ ካውንተር እና ኬጂ ከነ ግራናይቱ ጋር፣ ንቃይ የብረት በሮች፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የጥበቃ ቤቶች፤ የጣራ ቆርቆሮዎች፤ የባንኩ የቅርንጫፎች ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፤ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፤ አሮጌ ጋዜጣዎች፣ የኔት ወርክ ኬብሎች (UTP) እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል: -

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ሱሉልታ ሹፉኔ ልዩ ቦታው የቻይና ጋራጅ አካባቢ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ የአነን ሰላሌ የወተት አምራቾች ቅጥር ግቢ ውስጥ እና ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገዱ ወደ ቀኝ 200 ሜ.ት ገባ ብሎ በሚገኘው የፕልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ከ ቀን ታህሳስ 3፣ 6፣ እና 7፣ 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  3. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
  4. ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልፅ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ መግለፅ ይኖርባችዋል።
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም ካርድ ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፖኦ ውርስ ይደረጋል።
  9. ጨረታው ረቡዕ ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ረቡዕ ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 0115576174 ፖ.ሣ.ቁ 16936

ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!

 

Save Tender