የደ/ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዘመን የግሬደር መኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዘመን የግሬደር መኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
- የVAT /ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የTin ተመዝጋቢ የሆነ፤
- በ2018 ዓ.ም ግብር በመክፈል ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤
- በ Online አቅራቢነት E-GP የተመዘገበና ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክሜንቱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከአረካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት በሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን ዋና ን /Original/ በመያዝ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ላይ በማድረግ አንድ ኦርጅናሉን እና 2 ሁለት የኦርጂናሉ ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግና ሙሉ አድራሻውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid security/ “CPO” ከታወቀ ባንክ በባንክ የተረጋገጠ /approved/ የተደረገ ቼክ፣ ህጋዊ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በአረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በግዥ ንብረት አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር -8 ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ያለመገኘታቸው የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን እስከ አረካ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 09 13 05 51 85 ላይ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
የወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
