Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address የሚገኝበት ልዩ ቦታ መጠሪያው ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ልዩ ስሙ የሺ ደበሌ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113839716
  • Website
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityሎት1 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት2 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ሎት3 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨታ ቁጥር 002/2018

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች

  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያለው
  • የወቅቱን የመንግስት ግብር የከፈሉ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ
  • የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ
  • በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ
  • ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ አቅራቢዎች የጨረታውን ሰነድ የሺ ደበሌ በሚገኘው ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናንስና ጽ/ቤት አዲሱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተገለጹትን መረጃዎች በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ሎት1 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት2 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ሎት3 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • የግዢ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  • ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 383 9716 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋም የተደራጁ ከሆነ በተቋሙ የበላይ ኃላፊ የተፈረመ ወቅታዊ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።

መ/ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ መጠሪያው ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ልዩ ስሙ የሺ ደበሌ

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender