በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ የይፋት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Yifat Polytechnic College (የይፋት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ የይፋት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ አሌክትሪክሲቲ እቃ፣ ሎት 3 ኮንስትራክሽን ህንፃ መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 4 የልብስ ስፌት እቃዎች፣ ሎት 5. ብትን የደንብ ልብስ፣ ሎት 6 የደንብ ጫማ፣ ሎት 7 የመኪና ጎማና ቸርኬ፣ ሎት 8 የፅዳት አቃዎች
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው
- የሚወዳደሩ ተጫራቾች የገዥው መጠን ከብር 200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር በሎት ወይም በጥቅል መሆኑን አውቀው ጨረታውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቹ የሞላውን የጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /አንኮንዲሺናል ባንክ ጋራንት ወይም በጥሬ ገንዘብ(መሂ) በኮሌጁ ሕጋዊ ደረሰኝ ኮፒ ማስያዝ እና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ከላይ በተገለጸው ከሎት 1 እስከ ሎት 8 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው የጨረታ ጊዜ ጸንቶ ከሚቆይበት 40 ቀን በኋላ ለተጨማሪ 20 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዋዋል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አቅርቦቱን ላከናወኑበት ክፍያ ሲጠይቁ በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይቻላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ከላይ በተገለጸው ከሎት 1 እስከ ሎት 8 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ቢሮ ቁጥር 0920476967/ 0962344169 ማግኘት ይችላሉ።
በሰ/ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ የይፋት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
