በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በደ/ወሎ/ ዞን በተንታ ወረዳ የተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 2 የኅትመት ሥራን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ደ/ወሎ ዞን የተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በደ/ወሎ/ ዞን በተንታ ወረዳ የተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 2 የኅትመት ሥራን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ከላይ በተጠቀሰው የአገልግሎትና የአቅርቦት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፊኬሽን ጨረታ ሰነዱ ላይማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ከፍለው ከተንታ ወረዳ የተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ መሂ/ክ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በተንታ የመ/ደ/ስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 104 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ማለትም በ9/4/2018ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡45 ሰአት ላይ ይከፈታል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 10/4/2018 ዓ.ም 3፡30 ሰአት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ልክ 4፡45 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ግን መ/ቤቱ ጨረታውን ከመከፈት የማይታገድ መሆኑ ይወቁ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ባሸነፋቸው እቃዎች 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዙ መሆኑን ይወቁ፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን በበዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይበተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- በእያንዳንዳቸው እቃዎች በጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን ተጫራች ሆስፒታሉ አሸናፊ አድርጎ የሚመርጥ መሆኑን ይወቁ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች በተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማንኛውንም ወጪ ሸፍኖ የማቅረብ ግዴታ አለበት
- አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርባቸውን እቃዎች በባለሙያ ሲፈተሹ በጥራትም ሆነ በመጠን ችግር የሌለበት መሆኑ ተረጋግጦ ተቋሙ እንደሚረከብ ይወቁ፡፡፡
- በተራ ቁጥር ከተገለፀው የእቃ ዝርዝር ውስጥ ለይቶ መሙላት ከጨረታው ውጭያደርጋል፣
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡:
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ተንታ ወረዳ ተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 0930285726 ወይም 0921425161 ወይም 0979521238 በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ደ/ወሎ ዞን የተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
