Tender Detail

Tender Details


የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ፣ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኮምፒውተሮችና ላፕቶፖችን፣ ሎት 4 የቢሮ ቋሚ እቃዎችን፣ ሎት 5 የላብራቶሪ እቃዎችን፣ ሎት 6 የስፖርት እቃዎችን፣ ሎት 7 የደንብ ልብሶችን፣ ሎት 8 የጥገና ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ፣ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኮምፒውተሮችና ላፕቶፖችን፣ ሎት 4 የቢሮ ቋሚ እቃዎችን፣ ሎት 5 የላብራቶሪ እቃዎችን፣ ሎት 6 የስፖርት እቃዎችን፣ ሎት 7 የደንብ ልብሶችን፣ ሎት 8 የጥገና ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 212 በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ወይም አገልግሎት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ክሊራንስ የሚያቀርቡ ፣ መሆን መቻል አለባቸው።
  3. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላና የጥቅል ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 212 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ትክክለኛ አድራሻቸውን ስማቸውን በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ምድብ ስር ለሚገኙት የሚጫረቱበትን እቃ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 219 መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታው ውጤት ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ማስገባት ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለትምህርት ቤቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃዎች ውል በመዋዋል የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ አጠቃለው ዕቃዎቹን በ10 ቀናት ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፣ አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ገቢ ካላደረጉ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.1% በየቀኑ በመቀጫነት ይሰላባቸዋል፡፡
  11. የንግድ ድርጅቶች ለጨረታ የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገፅ ስምና ፊርማ ማስገባት አለበት፡፡
  13. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  15. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ሲመልሱ የቴክኒካል ሰነዶቻቸውን እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ ከአንድ (1) ኮፒ ጋር በማያያዝ ማስገባት አለባቸው፡፡ ሲፒኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መግባት አለበት፡፡
  16. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ90 (ዘጠና) ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
  17. የጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በትምህርት ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር +251-112-75 93 28

+251-112-76 54 24 የመ.ሣ.ቁጥር፡-23351

አድራሻ፡- መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰትን ነጥቦች ማሟላት ይገባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታ ሰነዳቸው ከጨረታ ውጪ እንዲሆን እንገልፃለን፡፡

 

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አንደኛ መካከለኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

 

Save Tender