በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና እቃዎች፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አሽ/ተሽ/ ፍ / ቁ / ባ / ጉለሌ / ቅ/ ጽ / ቤት 2018/002
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡- ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና እቃዎች፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ ።
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ከአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 39 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት፡-
- ለሎት 1 ፣ 2 ፣ 4 እና 5 ለእያንዳንዳቸው በተናጥል የ2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር) CPO
- ለሎት 3 የ1,000 ብር (አንድ ሺህ ብር) CPO ለእያንዳንዳቸው በተናጥል አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- ባለስልጣን መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ግቢ ውስጥ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 39
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-154-66-06፣ 011-54-61-90 መጠየቅ ይቻላል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
