የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የደንነት መጠበቂያ እና የደንብ አልባሳት ግዥ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የደንነት መጠበቂያ እና የደንብ አልባሳት ግዥ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዢ ዴስክ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።
- ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ ለሎት 01 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሁለት ሺ ብር) ለሎት 02 የፅዳት እቃዎች ግዥ ብር 24,000.00 (ሃያ አራት ሺ ብር) ሎት 03 የደንነት መጠበቂያ እና የደንብ አልባሳት ግዥ ብር 35,000.00 (ሰላሳ አምስት ሺ ብር) ለሎት 04 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ብር 90,000.00 (ዘጠና ሺ ብር) ለ4ቱም ሎት ለየብቻ የተሰራ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከህዳር 21 ቀን 2018 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም፡፡
አድራሻ:- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደሞ ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ
