በአ/ብ/ክ/መንግሥት/በደ/ወሎ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአ/ብ/ክ/መንግሥት/በደ/ወሎ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ፍ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአ/ብ/ክ/መንግሥት/በደ/ወሎ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች
1. አላቂ የቢሮ እቃዎች
2. ህትመት
3. ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
4. የፅዳት ዕቃዎች
5. ኤሌክትሮኒክስ
6. የሕንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ
የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር የሚችሉ መሆን ይገልጻል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
3. የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
4. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
7. ተጫራቾች ሰነዶቹን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ከደ/ወ/ዞን ለገሂዳ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከከሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ 1% /አንድ ፐርሰንት/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው። የሚያስይዙት ሲፒኦ/ ቢድ ቦንድ ከሆነ ደግሞ የገቢ ደረስኙን ፎቶ ኮፒ ከተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ አስገብተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ/ አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በጥንቃቄ በታሽገ ፖስተ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኅዳር 18/3/2018 እስከ 3/4/2018 ዓ.ም በለገሂዳ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ ቢሮ ቁ/8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ወዲያውኑ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በይፋ ይከፈታል፡፡
11. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለናሙና ያስቀመጥናቸውን ዕቃዎች ከግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 8 በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ።
13. አሸናፊ የሆነ አካል የዕቃ ርክክቡን የሚፈጽመው በዚሁ በለገሂዳ ፍ/ቤት ነው፡፡ ውልም የሚወስድ በዚሁ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
14. ማንኛውም አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን ርክክብ ሲፈጽም ጥራቱ በባለሞያ ተረጋግጦ የታሸጉ ዕቃዎች ተፈተውና ታይተው ተቆጥረው ተለከተው መቅረብ አለባቸው፡፡ ጥራትቸውን ያልጠበቁ ከሆነ በ5 ቀናት ውሰጥ መተካት አለባቸው፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ/ቁ 0332412000/ወይም 0927412789 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአ/ብ/ክ/መንግሥት/በደ/ወሎ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ፍ/ቤት
