Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)
  • Address ሳርቤት አደባባዩን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፓልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910622700
  • Websitehttps://oromialand.et/
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security250,000 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Vehicle tire

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/05/2018 ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ጎማዎች ከህጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/05/2018 ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ጎማዎች ከህጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  • ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ውል ገብቶ በተባለው ጊዜ ውስጥ ጎማውን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ በCPO) ብቻ ለመወዳደር 250,000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የእቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንቶችን የራሳችውን የፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን እና የጎማው የቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒውን ዶክመንቱን በተለያየ ከርPO ጋር በአምስት (5) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልከ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ 0949445729/0910622700/0919 519951/0946653304

አድራሻ ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ

 

የኦሮሚያ መሬት ቢሮ

Save Tender