Tender Detail

Tender Details


በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

የጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጣ/ወ/ፍ/ግ/ፋ/ቡ 57 /18

 

በአ.ብ.ክ.መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

•        ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ 2,600 ብር

•        ሎት 2. የህትመት የጨረታ ማስከበሪያ 1,200 ብር

•        ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 ብር

•        ሎት 4. እንጨትና የእንጨት ውጤት /ፈርኒቸር/ እና የቤትና የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 1,562 ብር

•        ሎት 5. የፅዳት እቃ የጨረታ ማስከበሪያ 800 ብር

•        ሎት 6. የቋሚነት ባህሪ ያላቸው እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 300 ብር በማስያዝና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የተሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1ኛ. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣

2ኛ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ነበር ያላቸው፣

3ኛ. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4ኛ. የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5ኛ. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ አርጅናሉን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

6ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው በአንድ ፖስታ በማሸግ ፊርማ ፣ ሙሉ ስም ፣ የድርጅቱ ማህተም የተጫረቱበት የጨረታ አይነት ከፖስታው ጀርባ ላይ አድራሻቸውን በመፃፍ ጣ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እቃ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስገባት አለባቸው።

8ኛ. ጨረታውን ሲሞሉ በጠቅላላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለውና የማይነበብ ከሆነ የነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል።

9ኛ. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

10ኛ. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ስለመሆኑ ወይም ቫትን የማይጨምር ስለመሆኑ በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።ነግር ግን በግልፅ ካላስቀመጡ ግዥ ፈፃሚው መ/ቤቱ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ የሚወዳደሩ ይሆናል።

11ኛ. መ/ቤቱ በጠየቀው የግዥ ብዛት ላይ እስከ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነው።

12ኛ. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል። ነገር ግን በጨረታ መክፈቻው ቀን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አንታገድም። በተጨማሪም የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሰኞ በተመሳሳይ ሰዓት 4:30 ይከፈታል።

13ኛ. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሎት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ቀርበው ውል መግባት አለባቸው፡፡

14ኛ. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉበትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት ግቢ ድረስ ሊያቀርቡ ነው።

15ኛ. ጨረታውን የምናጫርተው በሎት ሆኖ በአማርኛ ቋንቋ ነው።

16ኛ. መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ፡- 0116800692 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን

ደ/ሲና

 

Save Tender