የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች እና ሎት 3. የበጎች መድሃኒትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የደብረብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል፡-
ሎት 1. የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፣ ሎት 2. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3. የበጎች መድሃኒትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
• በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በየዘርፉ አግባብ ያለው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በየዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ የካላንደር ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሸጡበትን ዋጋ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በማያያዝና በፖስታ በማሸግ በደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው የጨረታ ሰነዱ ላይ የሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ ይሆናል ። ጨረታው በዚሁ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
• ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ከ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
• የጨረታ ማስከበሪያ በቁርጥ በየሎቱ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
• ተወዳድረው የአሸነፉ ድርጅቶች ያሸነፉትን ንብረት ማዕከሉ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ አለበት።
• ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨርታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
• የቫት ተመዝጋቢዎች 50% ቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን ።
• የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከናወናል።
• ማዕከሉ ከላይ ለሚፈልጋቸው ግዥዎች በየዘርፉ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የሚያገለግል እስፔስፊኬሽን በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 681 14 63 ወይም 011 681 23 30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል
