Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ቤኬ/አጠ/2ኛ/ደ/ት 01/2018 ዓ.ም

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቤኬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

ሎት-1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት-2. አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-3. የደንብ ልብስ፣ ሎት- 4. የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣ ሎት-5. የደንብ ልብስ ሰፌት፣ ሎት-6. የቤተ – ሙከራ ኬሚካሎችና አፓራተስ፣ ሎት-7. የቤተ-መፅሀፍ መፅሐፎች፣ ሎት-8. ልዩ ልዩ ማቴሪያሎች ሎት-9. የህክምና እቃዎች (የቀይ መስቀል እቃዎች)፣ ሎት-10. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት-11. ፈርኒቸር

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ እና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በየሎቱ በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር የያዘ መረጃ ሰነድ ከት/ቤቱ ግዥ ከፍል በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ዋጋቸውን ከነ ቫቱ ሙላት አለባቸው።

ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከላይ ለተገለጹት ለሎት1. 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብቻ)፣ ለሎት2 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብቻ) ብር ለሎት 3. 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሺህ ብቻ) እና ለሎት4. 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብቻ) ብር ለሎት 5. 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ለሎት 6. 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብቻ) ለሎት 7.7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብቻ) ብር ለሎት8. 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብቻ) - ለሎት9. 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) ለሎ.ት10. 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብቻ) ለሎት11.15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብቻ) ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ እና ማምጣት አለባቸው።

ተጫራቾች ለሚጫረቱት ጨረታ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ከአሸነፉት የጠቅላላ ዋጋውን 10% /አስር ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርበታል።

አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው የትራስፖርት ወጪ ት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ድረስ ማምጣት እስቶር ማስገባት አለባቸው።

በጨረታው ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ቢጠየቁ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው።

የጥቃቅንና አነስተኛ የሆኑት ድርጅቶች ባመረቱት ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡

ጨረታው የሚዘጋው ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ማለትም በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ/ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ- ለሚ ኩራ ክ/ከ/ወ/06 አራብሳ ሰፈራ አደባባይ 500 ሜትር ገባ ብሎ ወይም እንጀራ መጋገሪያ ሳይት 3 መምጣት ይችላሉ።

ስልክ: 011 6 12 59 12/011 6 12 58 12

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

 

Save Tender