Tender Detail

Tender Details


የአምሓራ ሳይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የወረዳ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለማውጣት ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4. የመኪና እቃ፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ፣ ሎት 6 ክሎሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአምሓራ ሳይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አም/ሳ/ወ/ገ/59/2018

የአምሓራ ሳይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የወረዳ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለማውጣት ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4. የመኪና እቃ፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ፣ ሎት 6 ክሎሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፦

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው።

3. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታለመሳተፍ ከላይ ከተራቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል።

7. ማንኛውም ተጫራች በሰነድ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው::

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8, ማግኘት ይቻላል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በገንዘብ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጂናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡

11. አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል።

12. ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ በሎት ድምር ነው።

 

13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአም/ሳ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችል ሲሆን ከሎት 1 እስከ ሎት 5 የተገለፁት እቃዎች በቀን 28/3/2018ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል።

14. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው /በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡

15. የመከፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

16. ጽ/ቤቱ ለሚገዛው እቃ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡

17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334470005 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

18. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

20. አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች/አርጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም በየፑሉ በሚገኘው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን የአምሓራ ሳይንት ወረዳ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን

Save Tender