የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት የ2018 ዓም በጀት አመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ወረዳ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት የ2018 ዓም በጀት አመት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ /የቢሮ አላቂ ዕቃዎች/
- ሎት 2 የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት 4 የደንብ ልብሶች /ለዳኞች/
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸርና ሌሎች /
- ሎት 7 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን /ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን/ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ ያላቸው።
- የእገልግሎት መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር መወዳደር ለሚፈልጉት እያንዳነዱ ሎት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ/ ብር በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርብዎታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካለሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 4፡00 የጨረታ ሰነድዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በሎት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ይሆናል።
- የዕቃውን ማንኛውንም ማጓጓዣ ወጪ ችሎ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳዳር ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፡፡
- የካባውን የጨርቅ ናሙና ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 28 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335541147 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ወረዳ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት
