በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር ለተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር ለተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ
ሎት 1. የተለያዩ የፅሕፈት መሳሪያዎች፣
ሎት 2, የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣
ሎት 3. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (ፕሪንተር እና ዴስክቶፕ)
ሎት 4. የተለያዩ ብትን የደንብ ልብስ፣ የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እና ቆዳ ጫማዎች ! -
ሎት 5 ህትመት
ሎት 6 የተለያዩ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ።
1. በዘመኑ በዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ከ1-3 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. የእቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክበተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ (ሰ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የግዢ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰእት እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ከምሽቱ 11፡30 ሰእት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከምሽቱ 11፡30 ሰአት ላይ ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ማለትም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው።
11. የጨረታ መዝጊያውንና መከፈቻውን ከመንግሥት ሥራ ቀን ውጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ ቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል።
12.ተወዳዳሪ ድርጅቱ ያሸነፈበትን እቃዎች በተሬ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ከፍል ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ኃላፊነት አለባቸው።
13.ውድድሩ በጥቅል /በሎት ስለሆነ ተጫራቾች በከፊል መሙላት አይችሉም።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0961177912 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-ጨረታውን ስትሞሉ በጥቅል ዋጋ መሆኑን አውቃችሁ እንድትሞሉ።
አድራሻ፡- ተሬ ጤና ጣቢያ ከሸዋሮቢት ከተማ 18ኪ.ሜ ገባ ብሎ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀ/ወ/አስ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት
