በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት2 የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት3 የደንብ ልብስ ፣ የስፖርት ትጥቅ ቱታ እና የደንብ ጫማ፣ ሎት 4 የቢሮ የጽዳት እቃ አቅርቦቶችን፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የኮንስትራክሽን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2018
በአ.ብ.ክ.መ በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት2 የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት3 የደንብ ልብስ ፣ የስፖርት ትጥቅ ቱታ እና የደንብ ጫማ፣ ሎት 4 የቢሮ የጽዳት እቃ አቅርቦቶችን፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የኮንስትራክሽን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል።
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና ግብር የከፈለ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው
- በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት እቃዎቹን ወረዳው ድረስ የሚያቀርብና ሂሳቡን በስሙ የሚያወራርድ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቸው ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- የጨረታ ሰነዱን አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09/02 ድረስ በመገኘት ለእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ/ሎት/ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ ከጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ለእያንዳንዱ ዘርፍ የጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ፣ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው። ፅ/ቤቱ ናሙና በሚጠይቁ እቃዎች ላይ ናሙና ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ በመቆየት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ተከታታይ ቀን ይቆያል።
- በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ማብራሪያ፣ ጥቆማ ወይም ቅሬታ ካለ በህጉና በአዋጁ መሰረት አልብኮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19/1 በአካል ፣በጽሁፍ ወይም በስልክ መጠየቅ ይቻላል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0332150032/0032150009
በደቡብ ወሎ ዞን የአልብኮ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
