Tender Detail

Tender Details


በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በጣርማበር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ስር ላለው ለአርመንያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት በመደበኛ እና ከውስጥ ገቢ ከሚሰበሰብ ለአርመንያ የጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልገሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን እቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በጣርማበር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አርመንያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ግዥ/ንብ/ስስ01/2018 ዓ.ም

 

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በጣርማበር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ስር ላለው ለአርመንያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት በመደበኛ እና ከውስጥ ገቢ ከሚሰበሰብ ለአርመንያ የጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልገሎት የሚውል

ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን እቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1፡- የተለያዩ አላቂና ቋሚ ፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2፡- የህትመት ውጤቶች እና ተዛማጅ
  • ሎት 3፡- አላቂ የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 4፡- ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች
  • ሎት 5፡- የደንብ ልብስ /ለምሳሌ የተዘጋጁ አልባሳት ጫማ ብትን ጨርቅ የሀገር ውስጥ 6000 ቲትረን/
  • ሎት 7:- ኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ እቃዎች እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ስለዚህ
  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዝርዝር ጉዳይ የያዘ የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በአርመኒያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር ቀርበው በመግዛትና መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ያሉትን ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ስም ፊርማ አድራሻ ስልክ ቁጥር በማስፈር በፅርማኒያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ገዥ ንብ/አሰ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ያሉትን ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ስም ፊርማ አድራሻ ስልከ ቁጥር በማስፈር አርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡29 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡50 ጀምሮ በአርመንያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግዥ ንብ/አሰ/ር ይከፈታል ፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡29 ሰዓት ላይ ይታሽግና እና 4:50 ይከፈታል ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾች ምርጫ ሲፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንከ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ወይም በመስሪያ ቤቱ ዋና ገ/ያዥ በመሂ 1 በጥሬ ገንዘብ በምትወዳደሩበት ዘርፍ /ሎት/ የጠ/ዋጋውን 1.99% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማሸግ ማስያዝ ይኖረባቸዋል ::
  5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  6. ለበለጠ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይቻላል።
  7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116300215/0929484745/0997402530 ደውለ ይጠይቁ፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- ጥራት የጎደላቸውን ግብአቶች/ አገልግሎቶች እና ቁሳቁሶች በመስሪያ ቤቱ ተቀባይነት የለም።

 

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በጣርማበር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አርመንያ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

 

Save Tender