Tender Detail

Tender Details


የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአንኮበር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ለ2010 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ለበጀት አመቱ ለስራ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች ባሉት የተዘረዘሩ ግዥዎችን በሎት በማደራጀት በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ የአንኮበር ወረዳ ፍ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአንኮበር ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ለ2010 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ለበጀት አመቱ ለስራ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች ባሉት የተዘረዘሩ ግዥዎችን በሎት በማደራጀት በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ድርጅቶችን በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-

የፅህፈት መሳሪያ፣ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ ቋሚ እቃዎች እና አነስተኛ ቋሚ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ሲሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በየዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
  3. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. የግዥው መጠን በአንድ ሰነድ ላይ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻው በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ ላይ ሙሉ ስም የድርጅቱ ማህተም ከፖስታው ጀርባ ላይ አድራሻቸውን በመግለፅ እና የሚወዳደሩበትን የግዥ የሎት አይነት በመግለፅ አንኮበር ወረዳ ፍ/ቤት ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ በመቅረብ ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 10 /አስር ብር/ በመክፈል እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ከቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታውን ሲሞሉ በነጠላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ስለመሆኑ ወይም የማይጨምር ስለመሆኑ በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው። ካላስቀመጡ ግን ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ቫትን እንዳካተተ አድርጎ የሚወዳደር ይሆናል።
  11. መ/ቤቱ እንደ በጀት አቅሙ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. የጨረታው የመጨረሻ ማስገቢያ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ድረስ ብቻ ነው።
  13. ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻው ቀን ተጫራቾቾ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት እንታገድም፡፡ በተጨማሪም የጨረታው የመክፈቻው ቀን በስራ ቀን ላይ የማይውል ከሆነ በቀጣይ በሚመጣው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 25% በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው።
  15. ጨረታውን የምናጫርተው በአማርኛ ቋነቋ ነው።
  16. ጨረታውን የምናጫርተው በሎት ብቻ ነው።
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011623-00-1 በመደወል ማግኘት ይቻላል ፡፡

 

በሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ የአንኮበር ወረዳ ፍ/ቤት

 

Save Tender