Tender Detail

Tender Details


በአማሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወገዲ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት ስር ሪድ ፕላስ በጀት እቃ ግዥ ለኤሌክትሮኒክስ፤ ለአላቂ አቃዎች እና ህንጻ መሳሪያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የሀገራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወገዲ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት ስር ሪድ ፕላስ በጀት እቃ ግዥ ለኤሌክትሮኒክስ፤ ለአላቂ አቃዎች እና ህንጻ መሳሪያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋብዛል።

በዚህም መሰረት፡- ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ስራ ዘርፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  3. የግዥ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው የንግድ ስራ ፍቃድ ኮድ መሰረት ንግድ ፈቃዳቸውን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዕቃ ግዥ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእቃ ግዥ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ ለሞሉት ዋጋ ለኤክትሮኒክስ ለአላቂዎች እና ህንፃ መሳሪያ 1.1 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ማድረግ አለበት ለግንባታው ግን ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይገባዋል፡፡ ካለው ደገሞ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  14. ውድድሩ በጥቅል ድምር (ሎት) መሆኑን አንድያውቁትና የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት የሚጠበቅብዎት መሆኑን አይዘንጉ፡
  15. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 30 ቀን መሆኑ ይታወቅ፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

ወግዲ

 

Save Tender