Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ነገሮቸን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 6214 = መድሃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች እና የላብራቶሪ ሬኤጀንት
  • ሎት 2 6218 = የፅዳት እቃ
  • ሎት 3 6212 = ፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት 4 6213 = ህትመት
  • ሎት 5 6219 = አላቂ ቋሚ እቃ
  • ሎት 6 6255= የጭነት አገልግሎት የኦክስጅን ሲሊንደር፣ መድሃኒት እና ነዳጅ ማጓጓዣ
  • ሎት 7 6313= ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃ

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውየዘመኑን
  2. ግብር የከፋሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች እያንዳንዱን በአንድ ገፅ ወረቀት ፎቶ ኮፒ ተደርጎ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ
  5. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፍል ይህ ጨረታ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት ደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 111 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት በጠቅላላ ከሞሉት ዋጋ ላይ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ።
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብርት አስተዳደር ቡድን ዘወትር በስራ ሰአት ይህ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰአት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ወ/ዞን ጤና መምሪያ በደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር (111) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው ከታሽገ ከ30 ደቂቃ በኋላ 4፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. የጨረታ መክፈቻ ቀን በእለቱ ከስራ ሰአት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰአት ይከፈታል
  11. ጨረታው በሎት ስለሆነ በሁሉም እቃዎች ሳይዘለሉ መሞላት ይኖርባቸዋል፡።
  12. በጨረታዉ የሚቀርቡ እቃዎች ኦርጅናልና ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለባቸዉ።
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር (111) ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 15 77 84 18 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  14. አሸናፊ የሆነዉ ድርጀት ያሸነፈበትን እቃ ከሆስፒታሉ መጋዝን ገቢ ማድረግ አለበት።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የደላንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን

 

Save Tender