የሸገር ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለመ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሸገር ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለመ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት-1 ጽህፈት መሳሪያ
- ሎት-2 የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት-3 ቋሚ ንብረት (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፈርኒቸር፣ ካሜራ)
- ሎት-4 የመኪና ጎማ
- ሎት -5 የሕትመት ሥራ
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- በገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራብነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳርቤት ፑሽክን አደባባይ ኪ-አብ ሕንጸ 4ኛ ፎቅ በሸገር ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ከነቫት በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ (አስር) ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 5 ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የተጫረቱበትን ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በድርጅቱ ስም ከባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። የመክቻው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጽመው ለመ/ቤቱ ማምጣት አለበቸው።
- የተጠየቁት ዕቃዎች በሙሉ ደረጃቸውን የጠበቁና ኦርጅናል መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሸገር ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
