Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ የቢሮ መገልገያ ኤሌክሮኒክስ እና የጽዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Kombolcha College of Agriculture (ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ)


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ የቢሮ መገልገያ ኤሌክሮኒክስ እና የጽዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማለትም፡- ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ላብቶፕ ኮምፒውተርና ፕሪንተር) ሎት 2 ስቴሽነሪ፣ ሎት 3 የዳቦ መጋገሪያ ማሽን፣ ከኤሌክትሪክ የሚሰራ የእንጀራ ምጣድ፣ የሽንኩርት መፍጫ ማሽን እና የሻሂ ማሽን፣ ሎት 4 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5 የውሃ መስመር መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሪክ መስመር መለዋወጫ እቃዎች እና በሎት 7 የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ እቃዎች ሎት 8 ለተማሪዎች ምግብ ቤት ማብሰያ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን (ብረት ድስት) እና ሌሎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ከላይ ከሎት1 እስከ ሎት 9 የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማቅረብ አግባብ የሆነና በየዘርፉ እና በዘመነ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ በደንብ በሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር በተናጥል A4 ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውንና በየዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ከአንድ ዘርፍ በላይ ለምትሳተፉ ተጫራቾች ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትን ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬድት ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ዋጋ ግምት 1% ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15/3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በስራ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0335510186 /0335514206 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመስረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ (ወሎ)

 

Save Tender