በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረት፡-
- የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች በደዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
- የትምህርት እና ስልጠና መርጃ ዕቃዎች በደዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
- የተለያዩ የህሙማን ቀለብ በዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
- የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ አላቂ የቁሳቁስና ፕሮፓጋንዳ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች
- አግባብ ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የቫት ተመዝጋቢ
- የንግድ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- ካሽ ሬጀስተር ተጠቃሚ የሆነ እንዲሁም በብርሃንና ማተሚያ ድርጅት የታተመ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ የሚጠቀሙና ለህጋዊነት ማረጋገጨ ከገቢዎች ቢሮ የድጋፍ ደብደቤ ማቅረብ የሚችል
- ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን 03 ወር ያልሞላው ግብር መከፈሉን የሚያረጋግጥ የቫት ሪፖርትና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚገለፅ ማስረጃ የሚያቀርቡ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በቁጥር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ። በመክፈል በኦሮሚያ ክልል ምስ/ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ጉ/አርጆ ቀበሌ ልዩ ቦታው ደዴሳ ካንፕ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
ለጨረታ ማስረከቢያ /CPO/ መጠን
- ለተለያዩ የቢሮ ፅህፈት ማቴሪያል ----------------------------- 7,500.00
- ለተለያዩ የፅፈት መሳሪያና ለትምህርት መርጃ መሳሪያ --------------------- 16,000.00
- ለተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እና አላቂ የቁሳቁስና ፖሮፓጋንዳ ዕቃዎች --------- 9853.60
- ለተለያዩ የህሙማን ቀለብ ----------------------- 27567.72
- ጨረታው ማክሰኞ ህዳር 09 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ክልል ምስ/ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ጉ/አርጆ ቀበሌ ልዩ ቦታው ደዴሳ ካምፕ ምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ግዥ ቢሮ 06 ቁጥር ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ከማቅረባቸው በፊት የዕቃዎችን ሳምፕል በቅድሚያ በማቅረብ ከግዥ ፈፃሚው አካል ጋር መተማመን ላይ መድረስ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-17-10-13-60 ወይም 09-56-12-70-89 መደወል ይቻላል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል
