የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች
1. ሎት 1 የጽ/መሳሪያ 5. ሎት 5 የጽዳት እቃዎች
2. ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 6. ሎት 6 ፈርኒቸር /የቢሮ መገልገያ እቃዎች/ የውጭ
3. ሎት 3 የመኪና እቃዎች 7. ሎት 7 ፈርኒቸር /የቢሮ መገልገያ እቃዎች/ የሀገር ውስጥ
4. ሎት 4 የመኪና ጎማና ባትሪ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟማላት ይጠበቅባቸዋል
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin number/ ያላቸው
- የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በሰሜን ወሎ ዞን ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የፎቶ ኮፒና የፋክስ ቀለሞች ኦሪጂናል ስለመሆናቸው በሚወስደው ፕሪንተር ማስሞከር፣ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀን ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ውድድሩ በድምር ዋጋ /በሎት/ መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ከ1 እስከ 7 ላሉት ሎቶች ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሎት 1-7 ያሉትን የጨረታ ሰነድ (መጫረቻ ሰነድ ከ 29/02/2018 እስከ 15/03/2018 ድረስ በመምጣት ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ 15/03/2018 ዓ.ም ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ከጧቱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ከሎት 5 እስከ ሎት 7 ያሎት ሎቶች ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታቸው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን የመቀበል ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/፣ ከሎት 5 እስከ ሎት 7 ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1/ በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን/ በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረከቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ /ስርዝ ድልዝ/ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ-
- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0333311597 /2680 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
- ከሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሰጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል።
- ሳምፕል /ናሙና ታይቶ ዋጋ የሚሞላባቸውን እቃዎች ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሰረት የመ/ቤቱን ሳምፕል በማየት ዋጋ ሊሞላ ይገባል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ግልጽ ያልሆነለትን ነገር ደውሎ ግልጽ ካልሆነለት በስተቀር ያለ አግባቡ ዋጋ መሙላት የለበትም፡፡ በኋላ ለሚያቀርበው ጥያቄ ተቋሙ የማይቀበልና የተቋሙ ሃሳብ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
