Tender Detail

Tender Details


ለቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ የሚገዛው ተዛማጅ አገልግሎት

በቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/

ለቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ የሚገዛው ተዛማጅ አገልግሎት

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

የሚያሲዙት ሲፒኦ በብር

1

የአይቲ እና የኤሌክትሮኒክስ ለኢንተርኔት ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎች

25,000.00

2

እላቂ የቢሮ እቃዎች

10,000.00

3

አላቂ የጽዳት እቃዎች

10,000.00

4

ፈርኒቸርና ብረታ ብረት

10,000.00

5

የህትመት ስራዎች

5,000.00

6

ልዩ ልዩ የጥገና መሳሪያዎች

30,000.00

7

የተለያዩ መድሀኒቶች እና ሪኤጀንቶች

10,000.00

8

የደንብ ልብስ

10,000.00

9

የመኪና ኪራይ

5,000.00

 

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

5. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ./ CPO/ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቦሌ/ከ/ከተማ ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ አለማየሁ ህንፃ ፊት ለፊት ገባ ብሎ ወይም ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ 5ኛ ፎቅ መውስድ ይችላሉ፡፡

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል አርጅናል እና ኮፒ በጤና ጣቢያው ግዥ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስራ አንደኛው (11ኛው) የስራ ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው የሥራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተጫራቾች በተወዳደሩበት የእቃ አይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባሉት ሁለት ቀናት ናሙና የሚያስፈልጋቸው ሎቶች ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከሰነዱ ጋር የተያያዘውን ስፔስፊኬሽን ላይ ማህተም በማድረግ መመለስ አለባቸው ዘግይቶ /ሰዓት/ቀን አሳልፎ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

10. ጨረታው በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ቡድን ባዘጋጀው አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡

12. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚወዳደሩ ለሚወዳደሩበት ሎት አምራች ስለመሆናቸው የሚገልፅ ከአደራጃቸው ወረዳ በበላይ ኃላፊ ተፈርሞ ማምጣት አለበት፡፡

13.ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡

14. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ከቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

16. የተሰረዘ የተደለዘ ግልጽነት የሌለው የጨረታ ሰነድ ይሰረዛል፡፡

አድራሻ፡-ቦ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ ከመገናኛ ወደ ጎሮ በሚወስደው ጃከሮስ አለፍ ብለው አለማየሁ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ኮብል ገባ በማለት ወይም ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ከርስቲያን

አጠገብ 5ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን  ያነጋግሩን፡፡ ስልክ ቁጥር፡- 011-6-39-50-33

ሲፒአ ሲዘጋጅ ፡- በኤረር ጤና ጣቢያ በሚል ይዘጋጅ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የኤረር ጤና ጣቢያ

Save Tender