Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ሎት 1 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 2. ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 3. ኮምፒውተር ፕሪንተርና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 4. የሙሉ ቀን ሥራ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ከ12 እስከ 15 ሰው የሚጭን ሚኒባስ መኪና ኪራይ፣ ሎት 5. የደንብ ልብስ፣ ሎት 6. ቋሚ ዕቃ፣ ሎት 7. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 8. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 9. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት10. የደንብ ልብስ እና ሎት11. የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

 

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ሎት 1 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 2. ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 3. ኮምፒውተር ፕሪንተርና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 4. የሙሉ ቀን ሥራ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ከ12 እስከ 15 ሰው የሚጭን ሚኒባስ መኪና ኪራይ፣ ሎት 5. የደንብ ልብስ፣ ሎት 6. ቋሚ ዕቃ፣ ሎት 7. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 8. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 9. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት10. የደንብ ልብስ እና ሎት11. የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

በዚሁ መሰረት፡-

  1. ሎት 4 የሙሉ ቀን ሥራ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ፣ሊብሬ እና ሶስተኛ ወገን ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ሎት 1 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 2. ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት3. ኮምፒውተር ፕሪንተርና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት5. የልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ፣ ሎት6. ቋሚ ዕቃ ግዥ፣ ሎት7. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት8. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት9. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት10. የደንብ ልብስ፣ እና ሎት11. የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ግዥ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለህትመት ውጤቶች ብር 5,000.00፣ ለቢሮ ዕቃዎች (ወንበር ጠረጴዛ) ብር 5,000.00፣ ለኮምፒውተርና ፕሪንተር እና ሌሎች አገልግሎት ጥገና ግዥ ብር 5,000.00፣ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 15,000.00፣ ለፅዳት ዕቃዎች ብር 3,000.00፣ ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 5,000.00፣ የደንብ ልብስ ብር 3,000.00፣ የሙሉ ቀን የሰርቪስ አገልግሎት ግዥ ብር 3,000.00፣ የመኪና ጌጣጌጥና ቅባቶች ብር 5,000.00፣ የልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ብር 3000.00 እና ቋሚ ዕቃ ብር 30,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብቻ በመከፈል ከቅ/ጽ/ቤታችን የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ምድር ላይ ቢሮ ቁጥር 01 የግዥ ቡድን ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በ11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል እና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
  10. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለው ማለት አይችልም።
  11. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፡፡
  12. ጨረታውን ለማባዛት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል።
  13. ተጫራቾች ለምታቀርቧቸው ናሙናዎች የምታመጡበት ዕቃዎች ጠንካራ እና በቀላሉ ሊቀደዱ የማይችሉ መሆን አለባቸው።

 

አድራሻ፡- መገናኛ የካ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ ምድር ላይ ቢሮ ቁጥር 01 የግዥ ቡድን ከፍል

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ. 09 11-68-45-54 እና 09 22-73-84-63 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

 

የየካ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender