የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች፣ ሎት 2 የስቴሽነሪ እቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የቧንቧና የኤሌትሪክ እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ጌጣጌትጥ፣ ሎት 7 የቅድመ አንደኛ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፈርኒቸር እና የቢሮ መገልገያ ሼልፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት 1 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች፣ ሎት 2 የስቴሽነሪ እቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የቧንቧና የኤሌትሪክ እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ጌጣጌትጥ፣ ሎት 7 የቅድመ አንደኛ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፈርኒቸር እና የቢሮ መገልገያ ሼልፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን እቃ እና አገልግሎት ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተመሰከረ /CPO/ ለሎት 1 ብር 100,000.00፣ ለሎት 2 ብር 30,000.00፣ ለሎት 3 ብር 10,000.00፣ ለሎት 4 ብር 10,000.00፣ ሎት 5 ብር 10,000.00፣ ሎት 6 ብር 20,000.00፣ ለሎት 7 300,000.00 ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከቢሮአችን ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና በዚያው ክፍል በሚገኝ ከግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነዱን በሶፍት ኮፒ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ለሎት 1 እና ለሎት 7 ቴክኒካልና ፋይናሽል ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታ በመለየት አሟልቶ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን / በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወደ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት እቃዎችን እና አገልግሎት ቢሮው በመረጠው ቦታ እና መጋዝን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
በስልክ ቁጥር፡- 011 122 64 56
አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
