በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት፡- የደንብ ልብስ፣ ሎት2- የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት3- ህትመት ውጤቶች፣ ሎት4- የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5-የመኪና እቃዎች፣ ሎት6- ልዩ ልዩ እቃዎች ሎት 7- የቢሮ ማሽን ጥገና፣ ሎት8- የላተራል ጥገና/ ሎት9- የአይቲ ዕቃ ግዥ፣ ሎት10- የቋሚ ዕቃ ግዥ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት፡- የደንብ ልብስ፣ ሎት2- የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት3- ህትመት ውጤቶች፣ ሎት4- የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5-የመኪና እቃዎች፣ ሎት6- ልዩ ልዩ እቃዎች ሎት 7- የቢሮ ማሽን ጥገና፣ ሎት8- የላተራል ጥገና/ ሎት9- የአይቲ ዕቃ ግዥ፣ ሎት10- የቋሚ ዕቃ ግዥ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ለመሳተፉ የዘመኑ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዊንጌት አደባባይ ድንገተኛ እሳት አደጋ መከለከያ ጎን በሚገኛው ህንጸ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሀሳባቸውን የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታችሁን ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በግልጽ በመጸፍ የሚወዳደሩበትን ሠነድ ኦርጂናልና ኮፒ ለየ ብቻ እንድሁም የቴክኒክ ዶክሜንት ኦርጀናልና ኮፒ ለብቻ በማድረግ በታሸገ ፖስታ መ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን በተጨማሪም መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ብቻ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በተሳተፉባት አቅርቦት ላይ ለመ/ቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ናሙና ለማቅረብ እና ናሙና ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ እና የጥራት መለኪያ፣ ስፔስፍኬሸን በተጠቃሚ ምርጫ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ በጽ/ቤታችን ስም ማለትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎ ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸበት ከሳበተኛው ቀን በኋላ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ የመጫረቻ ዋጋውን 10% /አስር ፐርሰንት/ CPO በማስያዝ የውል ስምምነት መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው መ/ቤቱ የእቃ መጋዘን ውስጥ ማቅረብ የሚጠበቅበቸው ሲሆን እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- በጨረታው የአሸነፉ ድርጅቶች እቃውን ባያቀርቡ ወይም ውል አንዋዋልም ቢሉ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡ እንዲሁም መ/ቤቱ በግዢው መመሪያ መሰረት ክስ ይመሰርታል፡፡
- የጨረታውን ዋጋ 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ ጨረታው ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ - 011-2735558/011-273 27 64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
