የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን
ETHIOPIAN CAPITAL MARKET AUTHORITY
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ECMA/NCB/09/2018
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፦
1- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ /ብር _ በመከፈል ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ከፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
2- ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴከኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፤የግብር ከሊራንስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4- ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
5- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
6- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል፡፡
7- አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ ሁሉ በራሱ ትራንስፖርት ባለስልጣኑ ዋ/መ/ቤት ወይም አገልግሎቱ በሚካሄድባቸው ሌሎች ቦታዎቸ ሁሉ የማምጣት እና አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡፡
8- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክየተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴከኒከ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10-አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
11-ጨረታው ህዳር 09 ቀን 2018 ከሰዓት በ9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ9: 30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12-በጨረታው መከፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
13-ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14-ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ምናዬ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርከ፣ ክ/ከተማ ቂርቆስ ወረዳ 9 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡- 011-5-57-83-27 E-mail- Procurement@ecma.gov.et
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣንዎ
