ኢታብ ሳሙና ፋብሪካ ለቀጣይ ጊዚያቶች በጥናት የተደገፈና ዘመናዊ አደረጃጀትን ለመፍጠር እንዲረዳው ድርጅታዊ መዋቅር፤ የሰው ኃይል ፕላን፣ የደመወዝ ስኬልና የተለያዩ የሥራ መመሪያዎች ጥናት ለማዘጋጀት በዚህ አሠራር ልምዱ ባለውና በቂ የማማከር አገልግሎት መስጠት የሚችል አማካሪ ድርጅት ቀጥሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ETAB SOAP FACTORY (ኢታብ ሳሙና ፋብሪካ)
ኢታብ ሳሙና ፋብሪካ ETAB SOAP FACTORY
ንፅህናዎ ለጤናዎ!! For health!
የኢታብ ሳሙና ፋብሪካ ድርጅታዊ መዋቅር፤ የሰው ኃይል ፕላን፣ የደመወዝ ስኬልና የተለያዩ የሥራ መመሪያዎች ጥናት ለማዘጋጀት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢታብ የሳሙና ፋብሪካ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ፤ በአንዲት ኪራይ ቤት በጎጆ ኢንዱስትሪ ንግድ ደረጃ በ300,000 ብር መነሻ ካፒታል በአቶ እስክንድር ተስፋዬ ባለቤትነት በ1993 ዓ/ም የተቋቋመ የግል ድርጅት ነው።
ፋብሪካው ከባህር ማዶ የሚመጣውን የልብስ ማጠቢያ ሳሙና ፍላጎት በመቀነስ ብሎም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ወጪ በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በአገር ውስጥ በማስተዋወቅ፤ የተሻለ አሰራሮችን በመፍጠር የሚያደርገው ጥረትም ትኩረት የሚስብ ነው። ፋብሪካው ለቀጣይ ጊዚያቶች በጥናት የተደገፈና ዘመናዊ አደረጃጀትን ለመፍጠር እንዲረዳው በማሰብ በዚህ አሠራር ልምዱ ባለውና በቂ የማማከር አገልግሎት መስጠት የሚችል አማካሪ ድርጅት ከዚህ በታች የተቀመጡትን ስራዎች ማለትም :-
- ወቅቱ የሚጠይቀውን ድርጅታዊ መዋቅርና የአደረጃጀት ጥናት፣
- ከዚሁ የመነጨ የሥራ መመሪያዎች (ማኑዋልስ)፤
- ወጪ ቆጣቢ የሆነ የሰው ኃይል ፕላን እንዲሁም
- ተወዳዳሪ የሆነ የደመወዝ ስኬል ጥናት እንዲዘጋጅለት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከላይ በግልጽ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ጥናቱን ለማካሄድ የብቃት መስፈርቱን የምታሟሉ በቂ ክህሎትና ልምድ ያላችሁ የሥራ አመራር ወይም የንግድ ሥራ አማካሪዎች ድርጅቱ ያዘጋጀውን ቢጋር/ Terms of Reference/ ፋብሪካው በሚገኝበት ሀዋሳ ከተማ በመምጣትና የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አስር የስራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች ማለትም፤
መደበኛ ስልክ ቁጥር 046-220-75-33
ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ 0912-10-73-34
ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
