የማኢ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሁለት ሎት ማለትም የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ (ሎት 1) እና በአላቂ እና በሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ (ሎት-02) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት
የማኢ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሁለት ሎት ማለትም የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ (ሎት 1) እና በአላቂ እና በሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ (ሎት-02) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ፡-
- ሎት-01 የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ እና
- ሎት-02 የአላዊ እና የሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- የዘመኑን ግብር ከፍለው ንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ እና የታደሰውን ንግድ ፈቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ፡
- ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
- በአላቂ እና በሌሎች አላቂ ዕቃዎች ላይ ለምትወዳደሩ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤
- በተሸከርካሪዎች ጥገና ላይ ለምትወዳደሩ ጋራዦች (ተጫራቾች) ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የታደሰ የደረጃ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለሎት1 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለሎት 2 ብር 14,000.00 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ቢድ ቦንድ ከሆነ የሚያሲዙት ከ90 ቀን ያላነሰ ጊዜ ያለው ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) እያንዳንዱን ሎት በመክፈል ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 22 በመግዛት ለተሸከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታ (ለሎት 1) ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎችን በየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ሎት-01 (የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ ጨረታን) በተመለከተ በመጀመሪያ ዙር የሚከፈተው ቴክኒካል ዶክመንት መሆኑንና ቴክኒክ ግምገማው ከ50% እና ፋይናንሻል 50% የሚያዝ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ከ70% በታች ወይም ከ50% ከ35% በታች የሚያመጡ ተወዳዳሪዎች የዋጋ ሰነዳቸው የማይከፈት መሆኑን ጭምር እንገልፃለን፣
- ለሎት-02 (ለአላቂ እና ለሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ) ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ከ60 ቀን ማነስ የለበትም።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ በስልክ ቁጥር 046-556-16-45 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት
