Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መጋላ 2ኛ ደ/ት/ቤት/ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መጋላ 2ኛ ደ/ት/ቤት


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር መጋላ 2ኛ ደ/ት/ቤት/001/2018 ዓ.ም

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መጋላ 2ኛ ደ/ት/ቤት/ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሎት የዋስትና ብር

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ- ብር 19,000.00 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች- ብር 19,000.00 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች- ብር 25,100.00 (ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ብር ብቻ)
  • ሎት 4 የፅዳት እቃዎች- ብር 23,000.00 (ሃያ ሶስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 5 ልዩ ልዩ ዕቃዎች- ብር 15,800.00 (አስራ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ብር ብቻ)
  • ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች- ብር 9,052,26.00 (ዘጠኝ ሺህ ሃምሳ ሁለት ብር ከሃያ ስድስት ሳንቲም ብቻ)

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሚያሲዙት CPO ህጋዊ የሆነ ባንክ የተሰራ መሆን አለበት።
  7. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ሀገር ውስጥ ምርት ላይ የተሳተፉ መሆናቸውን ካላመጡ የሰነድ ማስከበሪያ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማሲያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።
  9. ማንኛውም ተጫራቾች ተወዳድረው አሸናፊ መሆናቸውን ከአረጋገጡ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተወዳዳሪዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲያቀርቡና ሚያቀርቡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  11. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  12. ጨረታው ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጋላ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል፤ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  13. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማህተም በማድረግና አስፈላጊ ሰነዶችን በሟሟላት በሁለት ኮፒና ኦርጅናል ኤንቨሎፕ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  15. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ መጋላ 2ኛ ደ/ት/ቤት ማስረከብ አለባቸው።
  16. ተጫራቾች የሚሞሉት የአንድ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡

የመስሪያ ቤቱ አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አጠገብ መጋላ 2ኛ/ደ/ት/ቤት

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 672

ስልክ ቁጥር 011-4-71-50-64/65

አዲስ አበባ

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መጋላ 2ኛ ደ/ት/ቤት

 

Save Tender