Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሀዋሳ
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-71-38
  • Website
  • Deadline11 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityቢሮ ጽህፈት መሣሪያዎችንና አላቂ ዕቃዎችን 20,000 (ሃያ ሺህ)፣ ለጽዳት ዕቃዎች 8,000 (ስምንት ሺህ) እና የደንብ ልብስ 10,000 (አስር ሺህ) ብር
  • opening date2025-11-11 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሀዋሳ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1፡- የቢሮ ጽህፈት መሣሪያዎችንና አላቂ ዕቃዎችን፣
  • ሎት2፡- የጽዳት ዕቃዎች እና
  • ሎት3፡- የደንብ ልብስ

በዚሁ መሰረት ከላይ ለተጠቀሱ ዕቃዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች-

  1. የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የዕቃ አቅራቢነት ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ያልታገደ የንግድ ፍቃድ ወይም ታግዶ የነበረ ከሆነ የእገዳ ጊዜውን ስለመጨረሱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው 4ኛ ፎቅ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቢሮ ቁጥር 113 ይከፈታል። ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቢሮ ጽህፈት መሣሪያዎችንና አላቂ ዕቃዎችን 20,000 (ሃያ ሺህ)፣ ለጽዳት ዕቃዎች 8,000 (ስምንት ሺህ) እና የደንብ ልብስ 10,000 (አስር ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በእራሳቸው ፈቃድ በጊዜው አለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት አያስተጓጉልም።
  9. የጨረታው አሸናፊዎች በውሉ መሰረት ግዥ የሚፈጸምባቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ አቅርበው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመዘረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የመ/ቤቱ አድራሻ፡- በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ፤ ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (SBC) ቢሮ ጀርባ ባለው የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ።

 

ለበለጠ መረጃ

ስልክ ቁጥር 046-212-71-38

 

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት (ሀዋሳ)

Save Tender