በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም:-
- የስቴሽነሪ /አላቂ/ ዕቃዎችን (የፕሪንተር ቀለም፣ ማስታወሻ ደብተር፣ ቦክስ ፋይል፣ ካኪ ፖስታ እና ሌሎች) የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኮምገ/ብግጨ/ዕቃ/01/2018
- የጽዳት ዕቃዎችን (የገላ ሳሙና፣ የዱቄት ሳሙና፣ ፈሳሽ የእጅ ሳሙና፣ በረኪና እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች) የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኮምገ/ብግጨ/ዕቃ/02/2018
- የስፖርት ትጥቆች እና ዕቃዎች (ማሊያና ቁምጣ፣ ታኬታ ጫማ፣ ቱታ ከነአላባሹ፣ የሻወር ፎጣ እና ሌሎችም) የጨረታ መለያ ቁጥር- ኮምገ/ብግጨ/ዕቃ/03/2018
- የቢሮ ዕቃዎችን (የኃላፊ ተሽከርካሪ ወንበርና ጠረንጴዛ፣ የባለሙያ ተሽከርካሪ ወንበርና ጠረንጴዛ፣ የእንግዳ ወንበር፣ የእንግዳ አግዳሚ ወንበር፣ የሰነድ መደርደሪያ የእንጨት ሸልፍ እና ሌሎችም) የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኮምገ/ብግጨ/ዕቃ/04/2018
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን (ላፐቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ዲጂታል ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው፣ ኤሲ፣ መቅረፀ ድምፅ እና ሌሎችም) የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ኮምገ/ብግጨ/ዕቃ/05/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ)፤ በአቅራቢነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለስቴሽነሪ/አላቂ/ ዕቃዎች 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር)፤ ለጽዳት እቃዎች 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር)፤ የስፖርት ትጥቆችና እቃዎች 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር)፤ ለቢሮ ዕቃዎች ብር 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) እንዲሁም ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞላው ዋጋ በተጠቀሰው ቦታ ላይ ታክስን አካቶ መሞላት አለበት፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚገኝበት ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንታቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውንና ኮፒውን የጨረታ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለፅ በኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተዘግቶ የሚከፈትበት ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጭ ዘግይቶ የሚቀርብ፣ የተሰረዘ፤ የተደለዘ ወይም በግልጽ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ዕቃዎቹን እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የጨረታ ሰነድ መቀየር፤ ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 033-351-26-49/ ወይም 033-551-51-27 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
