በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን የሀደሮ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚሰጡ ዕቃዎች ሎት 01 የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 03 ፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን የሀደሮ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን የሀደሮ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚሰጡ ዕቃዎች ሎት 01 የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 03 ፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፣ በአቅራቢዎች ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬትና የግብር ከፋዮች መለያ ሠርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ጥሪ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሎት ተከታታይ 15 ቀናት በስራ ሰዓት በመገኘት ከመ/ቤታችን በግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁ.01 የጨረታ ሰነዱን በ500 /አምስት መቶ/ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የዋጋ ቅናሽ (Discount) እስካልተጠቀሰ ድረስ የዋጋ ቅናሽ ብሎ መሙላት ቅናሹ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡
- ተጫረቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ሲሆን ኮፒውን ማስያዝ ያለበት ሁሉንም የህጋዊነት ፈቃድ ዶክሜንቶችን፣ ሲ.ፒ.ኦ እና የሥራ ዝርዝርና ዋጋን አካቶ መያዙን በማረጋገጥ በድምሩ ሦስት ፖስታ ለየብቻ በማሸግ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረገጋጠ ሲ.ፒ.አ፤ በጥሬ ብር፤በኢንሹራንስ እና በቦንድ በማስያዝ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ የሚከፈተው በቀን 09/03/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 4፡30 በጽ/ቤታችን ግ/ን/አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን አቅርቦቶች በአጭር ጊዜ አጠናቀው ማስረከብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው ያቀረበው ዋጋ መነሻ በማድረግ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን የሀደሮ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
