ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር CN/NCB/13/18
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎት የግዥ ዋና ከፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00 - 6፡00 እና ከሠዓት 7፡00 - 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት 2፡00 – 6፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ. የግ.ማ.
