Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጣቢያ ሎት 1፡- የደንብ ልብስ፣ ሎት 2፡- ደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 3፡-የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 5፡- ህትመት፣ ሎት 6 ፕላንትና ማሽነሪ (ቋሚ እቃ)፣ ሎት 7:- የአይሲቲ እቃዎች፣ ሎት 8:- አላቂ የህክምና መሳሪያዎች፣ ሎት 9፡- የሮቶ እጥበት እና የላቦራቶሪ ማሽን ጥገና አገልግሎት ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።

በየካ/ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ጉራራ ጤና ጣቢያ


 

1ኛ ዙር አጠቃላይ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጣቢያ ሎት 1፡- የደንብ ልብስ፣ ሎት 2፡- ደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 3፡-የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 5፡- ህትመት፣ ሎት 6 ፕላንትና ማሽነሪ (ቋሚ እቃ)፣ ሎት 7:- የአይሲቲ እቃዎች፣ ሎት 8:- አላቂ የህክምና መሳሪያዎች፣ ሎት 9፡- የሮቶ እጥበት እና የላቦራቶሪ ማሽን ጥገና አገልግሎት

ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  3. ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል (ለሎት 1፣3፣4፣6)
  4. ግብር የመክፈል ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን ማስረጃ የሚያቀርብ፤
  5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጉራራ ጤ/ጣቢያ ግዥ ክፍል ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ከ 17/02/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ ሃሙስ ጠዋት ከ2:30 - 6:00 እና ዓርብ ከ2፡30- 5፡00 እና ከሰዓት ከሰኞ-ዓርብ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 5,000.00 ብር (አምስት ሺ ብር) ሲፒኦ በማሰራት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ አንድ ተጫራች አንድ ሎትና ከዚያ በላይ የሚገዛ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሎት ሲፒኦ ማሰራት ይጠበቅበታል (ከሲፒኦ ውጭ የሆኑ ዋስትናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።)
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፖስታ ለይቶ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ 17/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ አስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡00 ድረስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ብረት ድልድይ የሃ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ጉራራ ጤ/ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዥ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤
  8. ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፤
  9. ተጫራቾች ከውድድር በኋላ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉት እቃ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን በ01/3/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በጽ/ቤቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910275044 /0913062744/ መደወል ይቻላል።

አድራሻ፡- ፈረንሳይ ለጋሲዮን ብረት ድልድደ የሃ ት/ቤት ፊት ለፊት

 

በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት የጉራራ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender