ዴስክ ግ/ጨ C004/2018 በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ከ/ጦር መምሪያ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የፅህፈት፣ የፅዳት፣ የህሙማን ማገገሚያ እና የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር:- 104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር ግዥ
ዴስክ ግ/ጨ C004/2018
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ከ/ጦር መምሪያ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የፅህፈት፣ የፅዳት፣ የህሙማን ማገገሚያ እና የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በሚጫረቱባቸው የጨረታ አይነቶች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብርመከፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ /ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡
5. አሸናፊ ድርጅቶች ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ያሸነፉትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ 90 ቀናት ድረስ መቆየት ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የዕቃውን ሙሉ ስም፣ የተሰራበትን ሃገር እና የጥራት ደረጃውን (Specification) አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾቹ ስለሚጫረቱባቸው ለአያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ላይበተገለፀው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የእቃውን አይነት ኤንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መምሪያ ጋር የማይመለስ ብር 200.00 በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ኦሮሚያ መደበኛ ፖሊስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ የሚገባው ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን በእለቱ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቡልቡላ ኦሮሚያ መደበኛ ፖሊስ ኮሌጅ ውስጥ በ5፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይበተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. የመጫረቻ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ከ15/02/2018 ዓ.ም እስከ 29/02/2018 ዓ.ም ድረስ ነው፡፡
11. የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር መምሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር-09-63-61-99-80 ወይም 09-12-32-12-99 ይደውሉ፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ104ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር
