የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም፣
- ሎት 1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2. ቋሚ እቃ
- ሎት 3. የደንብ ልብስ
- ሎት 5. የመኪና ጎማ እና ጌጣጌጦች
- ሎት 6. የህትመት ሥራዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ
- ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የኢፌዴሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና Tin No ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ /Finacia/ ሰነድ እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፤ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡
- ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0904159873/0913149064 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅ/ጽ/ቤታችን ፋይናንስ ክፍል በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
