Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
  • Address Bole Road, behind Dembel City Center, Seid Yassin Building., addis ababa,Ethiopia, Phone: 011-1-569992
  • Websitehttps://commercialnominees.com/
  • Deadline06 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security100,000 (መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-06 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።

Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/13/18

 

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለሚገኙ የድርጅቱ ቋሚ ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ ኮት እና ሱሪ)

ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ስርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በስም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሠዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት 2:00-6፡00) ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ

ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 011-1-569992

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

Save Tender