የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ር/መስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ር/መስተዳደር ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ር/መስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተመለከተውን
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃ
- ሎት 3 ጃኩዚ ስቲም እና የሻወር አገልግሎት የሚሰጥ ባዝታብ ከነሙሉ አክሰሰሪ
- ሎት 4 ፈርኒቸር (ሮያል ኪንግ መጠን ያለው በእጅ የተሰራ ወንበር) ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በዘርፉ በተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ የመንግሥት ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ማቅረብ የሚችል
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የመወዳደሪያ ዋጋው ቫትን ጨምሮ በግልፅ መፃፍ አለበት
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ cpo 20,000 (ሃያ ሺ) ብር ማስያዝ ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከተራ ቁጥር 1-4 ድረስ ላሉ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቀርበው ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት 5፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ በማቅረብ ያስረክባል፡፡ አስቀድሞ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ዝርዝር የጨረታ ሂደት በጨረታው ሰነድ መመሪያ ላይ ተገልጧል፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር- 046-2124290/91
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ር/መስተዳደር ጽ/ቤት
