Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 226 3095
  • Websitehttps://amharaforest.gov.et
  • Deadline04 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-11-04 00:00:00
  • Categories Forest And Tree Sales

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሁለቱ ወገዳሜ ቀበሌ ገልዳ ማዶ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 889.41 ሜ/ኩብ እና ቀይ ባህርዛፍ 351.84 ሜ/ኩብ በድምሩ 1.241.25 ሜ/ኩብ ቁም ደን እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬና ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች ባሉ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኝ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 3,209.30 ሜ/ኩብ፣ የነጭ ባህርዛፍ 17,422.43 ሜ/ከብ፣ የፈ/ግራር 16.25 ሜ/ኩብ እና የወደቀና የደረቀ 6.82 ሜ/ኩብ በድምሩ 20,654.80 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)


የቁም ደን ምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሁለቱ ወገዳሜ ቀበሌ ገልዳ ማዶ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 889.41 ሜ/ኩብ እና ቀይ ባህርዛፍ 351.84 ሜ/ኩብ በድምሩ 1.241.25 ሜ/ኩብ ቁም ደን እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬና ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች ባሉ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኝ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 3,209.30 ሜ/ኩብ፣ የነጭ ባህርዛፍ 17,422.43 ሜ/ከብ፣ የፈ/ግራር 16.25 ሜ/ኩብ እና የወደቀና የደረቀ 6.82 ሜ/ኩብ በድምሩ 20,654.80 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቶች:-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ VAT ምዝገባ የምስከርወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ለጨረታ የቀረቡትን ቁም ደን /ምርቶች/ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ::

4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን በኦርጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚዝዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ፧ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች «የቁም ደን የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ, ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጅ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡

7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡

8. ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ከፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

11. ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095 ደ/ታቦር 0584410306፣ ደ/ብርሃን 0116375017፣ እንጅባራ 0582270485፣ ደ/ማርቆስ 0588719004፣ ኮ/ቻ 0914716636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት

Save Tender