በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ Gravelea roubsta" ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
OFWE/GU- 03/2019
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ Gravelea roubsta" ድብልቅ ግንድላ እና የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ቦሬ ድስትሪክት፤ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ምዕራብ ወለጋ ድስትርክት፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጃሎ ሙክታር ዲስትሪክት እና አርሲ ቅ/ጽ/ቤት አዳባ ዶዶላ ዲስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና "TIN number" ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ አይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ፤ እና አርሲ ቅ/ጽ/ቤት ነጌሌ አርሲ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ጨረታው የምዘጋበት እና የምከፋት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፤ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 በመደወል ማጠየቅ ወይም "www.oromiaforest.et ድህረ-ገፅ ማጎብኘት ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Sale of standing eucalyptus and mixed timber lots (eucalyptus, Grevillea robusta, and Bahir zaf) by open bid across Oromia forest offices. Open to firms and individuals with renewed timber and sawmill trade licenses and VAT/TIN registration.
