Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 6 18 61 25
  • Website
  • Deadline19 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500(አምስት መቶብር )
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ (CPO), ለ30 ቀናት የፀና
  • opening dateጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Forest And Tree Sales , Agricultural Products

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ


የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - የም/ዘ/አ/ዘ/ግጨ/ሽ01/2019

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን-የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሀሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30 ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-5:30፣ ከሰዓት በኋላ ከ7:30-10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ሰዓት በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊትለፊት በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 እንዲሁም በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ንግድ ምክር ቤት ጎን አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት በምርጥ ዘር አቅርቦት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110ና በኮርፖሬሽኑ አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
አዲስ አበባ 0114-70-84-75/0116-66-23-90
አዳማ 0221-11-21-22/0221-11-31-56
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation's Quality Seed Supply Sector, Adama branch, seeks to sell various types and grades of natural gum products via competitive bid. Eligible bidders must have a renewed trade license, TIN, VAT registration, commercial registration, and bid participation clearance. Bidders may bid for all or part of the listed products.
Save Tender