በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
- አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ልዩ ልዩ ህትመቶች
- ቋሚ እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- ልዩ ልዩ እቃዎች
- የቢሮ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 - 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከፍ/ቤቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 20 ከተራ ቁጥር 1- 4 ለተዘረዘሩት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከተራ ቁጥር 5 - 7 ለተዘረዘሩት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋውን ቫቱን ጨምሮ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመ/ቤቱ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት በደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ደ/ብ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 011 681 61 85 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
