የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንበ ልብስ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/UE/156/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንበ ልብስ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃውን ዓይነት |
የፕሮጀክት ስም
|
የጨረታ ቁጥር
|
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት
|
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1 |
የደንብ ልብስ |
ዋና መ/ቤት |
DCE/UF/156/2025
|
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም 4:15 ሰዓት |
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት
|
50,000.00
|
ስለሆነም፡-
1.ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስከር ወረቀት (ታከስ ከሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቶች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ…ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንከ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) 120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያቀርቡበት ወቅት ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች አብሮ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ
ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ:- Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁጥር 0114-40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ
