በ2018 በጀት ዓመት በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በ2018 በጀት ዓመት በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
- የተለያዩ ዓይነት የጽ/መሣሪያዎች
- የደንብ ልብስ የሲቪል /ወታደራዊ/
- ፈርኒቸሮች /የቢሮ መገልገያ
- ኤሌክትሮኒክስ /የቢሮ መገልገያ
- የተለያዩ ዓይነት ሞተር ሳይክሎች
- የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እንዲያስችል የሚወዳደሩ ድርጅቶች
- በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት ያላቸው
- የዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው እና ዕቃውን ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ
ድርጅቱ ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን 3,000 /ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸውና የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዱ ኦርጅናል ከላይ የተገለጸውን ማስረጃዎች ጭምር በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁ 14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። ጨረታውም በ16ኛው የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዪ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በዕለቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉለውም።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋ/ል/ጽ/ቤት
